♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 59..
.
.
ዳኞች እና ታዳሚዎች አጨበጨቡ የሽልማቱ ሰአት ደረሰ። እና ያለ ምንም ተቋውሞ ሰአሊ ቀመር በሚገርም ውጤት አሸነፈና የብር እና የዋንጫ ሽልማት አገኘ። ሁሉም ተደሰቱ ቀመር " በሉ ላድርሳቹ ወደ ቤት" አላቸው የመውጫ በሩ ላይ ሲደርሱ። ያቤፅም " አያስፈልግም ጓደኛዬ እናመሰግናለን መኪና ይዘናል" አለው። ደራሲው መጥቶ ሁሉንም ሰላም አላቸውና "በጣም ጥሩ አሳዛኝ ታሪክ ነበር ያሳለፋችሁት" አላቸው። ስአሊ ቀመረም "ልክ ነው ህይወት ትፈትናለች ግን በእዚህ መጠን ስትፈትን ከባድ ነው በእነሱ ታሪክ እኔም አልፎልኛል እና ህይወቴን የሚቀይር ገንዘብ አግቻለሁ" አለ። በፀሎትም ለሰአሊው ቀመር " ልክ ብለካል አሁን እኛም ያገኘከውን ገንዘብ በጭራሽ አንጋራክም ያንተ ስኬት ለእኛ በቂ ነው" አለች።
ፅናትም "እህቴ ልክ ናት እኛ በህይወት አጋጣሚያችን ባገኘናቸው ሰዎች አሳቦ አምላክ በቂ የሆነ ሀብት ከጤና ጋር ሰጥቶናልና ካንተ ደስታክን ብቻ ነው የምንፈልገው።" አለችው።
ደራሲ መሀመድ ሳላዲንም "ጥሩ አስተሳሰብ የያዛቹ ናቹሁ እኔ ኑሮዬን ጠቅልዬ ከእዚህ ሀገር ልወጣ ነው። ባለኝ ጊዜ ሙሉ ታሪካችሁን መስማት ከባድ ነው በእረግጥ በሚገረም መልኩ ሰአሊው ስለ ህይወታቹ ባጭሩ አስረድቷል ግን ደሞ ሙሉን በደንብ ብሰማው ምኞቴ ነው" አላቸው። ያቤፅም "ሁሉን ነገር የፃፍኩበት ማስታወሻ አለኝ እሱን ልሰጥህ እችላለሁ ከዛ ኮፒ አረገክ መውሰድ ትችላለህ አለው። ደራሲውም ስልኩን ለያቤፅ ሰጥቶት ሄደ። እነ ያቤፅም ወደ ቤታቸው ሄዱ።
፨፨፨
ከ 8 አመት በኋላ ፨፨፨
አንድ የሚያምር ቤት ሳሎን ውስጥ የፅናት በቬሎ ያገባችበት ፎቶ በትልቁ ግድግዳ ላይ ተሰቅሏል።
ፅናት መኝታ ቤት አልጋ ላይ ከልጅዋ ቤካኔ ጋር በትራስ እየተደባደበች (እየተጫወተች) ነው። በድንገት ጨዋታውን አቁመው አልጋው ላይ በጀርባቸው ተንጋለው እኩል "ኡፍፍፍፍ" አሉ ፅናት "ልጄ" አለችው ቤካንም "አቤት ማማ" አላት። የህይወት ጣእምን በምን ልንለካ እንችላለን " አለችው። ቤካንም "በምንወዳቸው ሰዎች" አላት።
"የህይወት መጥፎ ጣሙዋንስ" ስትለው "በሚፈትኑን ሰዎች" አላት። ፅናት ጎበዝ ልጄ ብላ ግንባሩን ሳመችው። በድንገት ጩከት ሰሙና ተደናገጡ።
ቤካን እና ፅናት ተደናግጠው ወደ ሳሎን ሄዱ። በፀሎት ፣ ፍፁም እና ትንሽዬ የምታምር የበፀሎት ልጅ ሳሎን ቁጭ ብለው አገኟቸው። ቤካን "እኔ እና ማማ ጩከት ሰምተን ነበር የመጣነው" ሲል ትንሽዬዋ የበፀሎት ልጅ ሊባኖስ "እናቴ ናት የጮኸችው" አለች። ፍፁምም
"አዎ በረንዳ ላይ ውሀ ነበር እሱ አንሸራቷት ነበር ግን እኔ ደግፌ አስቀረዋት" ሲል። ትንሿ ሊባኖስ ከአባትዋ ፍፁም ጋር ሳቁ ቤካንም ሳቀ።
ከውጪ የመኪና ክላክስ ተሰማ።
ቤካን "ባባ መጣጣ ብሎ ሮጦ ሄደ" ፅናም "ቀስ በል ቤኮ እንዳትወድቅ" አለችው እና ሶፋው ላይ ተቀምጣ "እሺሺ እንዴት ናቹህ" አለቻቸው። በፀሎትም "ደና ነን እህቴ አንቺስ" አለቻት። "እኔን ተይኝ ያው እሁድ ለእኔ ከቤካን ጋር የምዳረቅበት ቀን አደል" አለች። ትንሽዋ ሊባኖስም "ማሚዬ ዛሬ ደብሯታል ልክ እንደ አሻጉሊት ኩርፍ ብላ ተቀምጣ አባቢ ሲያወራት እ ፣አዎ ፣በጣም፣ ልክ ነክ፤ ኧረ እያለች ነው የመጣችው።" አለች። ፍፁም ፅናት እና በፀሎት ሳቁ ፅናት "የእኔ ቅመም" አለቻት።
ቤካን ወደ ሳሎን መጣና "ታታታ አባ መጣልኝኝኝ "አለ የያቤፅን እጅ እየጎተተ እያስገባው። "ኦኦኦኦ እስኪ ተመልከቱ የእኔ ቆንጅዬ አማች ከባልዋ እና ከትንሼዬዋ ልእልት (ከልጅዋ) ጋር መታለች።
የእኔ ልዩ እና ቆንጅዬ የልጄ እናትም አለች"
አለ። ቤካንም "አሀ ቆይ እኔስ" አለው። ያቤፅ ፈገግ ብሎ "ገና መቼ ተናግሬ ጨረስኩኝ ውዱ ልጄ የእኔ ትንሹ ልኡል ቤኮ ደሞ እንደ እሳት ፈጥኖ እየሮጠ ከበር ተቀበለኝ" አለ። ሁሉም ከት ብለው ሳቁ።
አሁንም የመኪና ክላክስ ተሰማ። ቤካን "ውይ አያቴ እና ቅድመ አያቴ መጡ" ብሎ እሮጦ ሄደ። ፅናት "ወይ አምላኬ ምን አይነት ቀውስ ልጅ ነው የወለድኩት " ስትል በፀሎት "ኧር የእኔዋ ቃጠሎ ምላሳምስ" አለች። ያቤፅ "በሉ በሉ ከልጆቹ ወረድ መጣው ልብሴን ቀይሬ" ብሎ ሄደ።
ቤካንን ስማ አቅፋው የያቤፅ አያትም ከኋላ እየተከተሉ ተከታትለው ገቡ። ሁሉም ብድግ ብለው ሰላም አሉዋቸው። ቤካን "ውይ አያቴ ሶሲ ዛሬ ደሞ ቆንጅዬ ሆነሽ ፉንጋዋን እናቴን በልጠሻታል " አላት። ሶስና ክትክት ብላ ስቃ "በምን" አለችው። ቤካንም "በፉንጋነት" አለ። ይህ የተለመደ የሚያዝናና የሁለቱ የሁል ጊዜም ንግግር ነው።
ቤካን ወደ ያቤፅ አያት ሄዶ አጠገባቸው ተቀመጠና "ቅድም አያቴ ዛሬ ደሞ አምሮብሀል" አላቸው። እሳቸውም በምን አሉት። ቤካንም "በበበ በ በቃ ተወው" ብሎ ምላሱን ነከሰው ይህ ደሞ ቤካን ሁሌም ከቅድመ አያቱ ጋር የሚያደረገው ንግግር ነው። ቤካን እንዲ ነው ልክ እንደ አባቱ ነው ነገሮችን የሚያከናውነው መልኩም አባቱን ቁጭ ነው። ሰራተኛዋ ለፅናት ምሳ እንደደረሰ ምልክት ሰጠቻት። ፅናትም በሉ ተነሱ ምሳችንን እንብላ ምሳ ደርሷል" አለች ሁሉም ተነስተው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ተቀመጡ።
ቤካን ልክ ሊበሉ ሲሉ "ቆይ ፀሎት" አለ። ሁሉም ፈገግ ብለው ፀልየው መመገብ ጀመሩ።
እየበሉ ያቤፅ መጣና "መልካም ምግብ" ብሎ ሊበላ ሲል። ቤካን "ባባ እንዲባርክህ መጀመሪያ ፀልይ" አለው። ያቤፅም ፈገግ ብሎ ፀልዮ መብላት ጀመረ። ትንሽዋ ሊባኖስ "ስማ ቤካን ያንን ታሪክ ትጨረስልኛለህ" አለችው። ቤካንም
"ምግብ ላይ ቁጭ ብለሽ ስለተረት መፅሀፍ አታውሪ ብይና ጠይቂኝ " አላት።
በፀሎት ሳቀች። "ቤካን ምግብ ክብር ነው አክስቴ አንቺ እና ልጅሽ ዛሬ ገበታ ላይ ጥሩ ፀባይ አላሳያችሁም" አለ። ሁሉም በልተው ጨረሱ እና ከጠረጴዛው ተነሱ።እና ሶፋው ላይ ተቀመጡ።
ፅናት እና በፀሎት ሶስና የሰጠቻቸው የየራሳቸው ቤት ውስጥ ነው የሚኖሩት። በፀሎት "ዛሬ እራት እኛ ቤት ነን ከዛ በፊት ለልጆቻችን እና ለእናንተ ከእህቴ ጋር የምናሳያቹህ ነገር አለ።" አለች።
ሁሉም "ምንድነው ምንድነው" አሉ። ፅናትም "እሱን ታይውታላቹ አሁን ለመውጣት ያልተዘጋጀነው እኔ ፣ ልጄ እና ባሌ ነን ስለዚህ ተዘጋጅተን እንመጣለን "በሉ ኑ" አለቻቸው ያቤፅ እና ቤካንን ሁለቱም ፅናትን ተከትለዋት ሄዱ እና ለባብሰው ወጡ። ቤካንም "ልክ እንደ እናቴ እና አክስቴ አይነት ቆንጆ አይቼ አላቅም" አለ። ትንሽዋ ሊባኖስም "እህ እኔስ" ስትለው። ቤካን "አንቺም ቆንጆ ነሽ ያው አንቺንም ይጨምራል ልእልቷ" አላት።
ሁሉም በትልቅ መኪና ውስጥ ገብተው በሹፊር መጀመሪያ ወደ ጋሽ በሬሳ ቤት ሄዱ። አሁን የጋሽ በሬሳ ቤት ቤት አደለም አሁን ሁሉም ነገር ተቀይሮ የሀይምሮ ህሙማን ትልቅ ሆስፒታል ሆኗል። የሆስፒታሉ ስም ህይወት ነው። ህይወት የሀይምሮ ህሙማን ድርጅት። ይላል። ፅናት በእዚህ ድርጅት ውስጥ በዋናነት ትሰራለች። ፅናት "ሊባቲ ትንሽዋ እና ቤካን ይህ ሀኪም ቤት ማለት ባለፈው የነገርኳቹ ታሪክ ውስጥ የነበረ የጋሽ በሬሳ ቤት ነው። ጥቂቱን ክፍል እኔ ጋሼ ለሰጡኝ መፅሀፉ መመራመሪያ " ነው አለቻቸው።
ቤካንም "እንዴ ማማ የነገረሽን ታሪክ እውነተኛ ነው ማለት ነው " አለ። በፀሎትም "አዎ እናትህ የነገረችህ እውነተኛ ታሪክ እንጂ ተረት አልነበረም " አለችው። ቤካንም "ስለዚህ ቆነጃጂቶቹ እናንተ ናቹሁ።
.
https://vt.tiktok.com/ZSxTyu1YD/የመጨረሻ ክፍል 60 አርብ 2:00 ሰአት