ጥቅምት 8
Oct 18
ኢየሱስ እንደ ነቢይ
ሙሴ እንዲህ ሲል ተነበየ፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል፣ ከወንድሞችህም እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልና፣ እርሱንም ታደምጣለህ” (ዘዳ 18:15)። ያ ነቢይ ማን ነው? የእግዚአብሔር ቃል ራሱ ግልጽ አድርጎታል። ወደ ኢየሱስ ወደ እራሱ እያመለከተ ነው። “ሙሴም ለአባቶች ‘ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሳኝ ከወንድሞቻችሁ ያስነሳላችኋል በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት’ አለ” (የሐዋ 3:22፣ዮሐ 6:14ንም ይመልከቱ)። የኢየሱስ የነቢይነት ሚና ምን ነበር? ኢየሱስ ይህን ጥያቄ እንዴት መለሰ? (ማቴ 16:13-16፣ማር 8:27-29፣ሉቃ 9:18-20)።
Save Notes
የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ ያመላከቱት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መሲሁ ነበር። በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ የመሲሐዊ ትንቢቶቻቸው ፍጻሜ መሆኑ ተገለጸ። በሉቃስ 24:13-15 ላይ መሲሐውያን ነቢያት የተናገሩለት እርሱ ራሱ መሆኑን መሰከረ።
እንዲያውም በዮሐንስ 1:1-5 ስለ ቃሉ የተሰጠው መግለጫ ለማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ወይም ለሰብዓዊ ነቢይ አይመጥንም (አይገጥምምም)። ቃሉ ፈጣሪ መሆኑ ተገልጧል፦ “ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳች እንኳን ያለ እርሱ አልሆነም”(ዮሐ 1:3)። ይህ ማለት የተፈጠረውን ሁሉ፣ 93 ቢሊዮን የብርሃን ዓመታት (light years) ስፋት እንዳለው የሚገመተውን አለማትን በሙሉ ፈጠረ ማለት ነው።
በዘፍጥረት 1 ላይ “እግዚአብሔርም አለ” በሚለው በእያንዳንዱ ንግግር ኢየሱስ ሲናገር እንሰማለን። “ብርሃን ይሁን” ያለው(ዘፍ 1:3) እርሱ እራሱ የዓለም ብርሃን ነው (ዮሐ 1:4)። ከዚህ የተነሳ በመዳን ዕቅድ መሠረት የምድርን ጨለማ ገፈፈ (ዮሐ 1:4-5)።
የእግዚአብሔር ትንቢታዊ ቃላት የታመኑና እውነቶች ናቸው። ለሚሰማቸው ሁሉ “ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ በጨለማ ስፍራ የሚያበራ ብርሃን” ናቸው (2ኛ ጴጥሮስ 2:19)። “የንጋት ኮከብ” የሆነው ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ ትንቢት ለዚህ የጨለማና የኃጢአት ምድር ማብራቱን ይቀጥላል። የዚያ ትንቢታዊ ብርሃን ምንጭ የሆነው የዘላለሙን መንግስት ያመጣል።
እስከዚያ ድረስ ግን ክርስቶስ በህይወቱ፣ በሞቱና በትንሣኤው አማካኝነት የዘላለም ህይወትን ተስፋ አረጋግጦልናል። ጥያቄው ግን የእኛ ለመቀበል የሚኖርን ፈቃደኝነት ብቻ ነው።
ፈጣሪው ኢየሱስ(ዮሐ 1:1-3) ኃጢአትዎትን ለማስተሰረይ በመስቀል ላይ መሞቱን ያሰላስሉ። ይህ አስገራሚ ክስተት(እውነት) እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እውነተኛነት ምን ያህል ያስረዳል? ፈጣሪው ኢየሱስ (ዮሐ 1:1-3) ኃጢአትን ለማስተሰረይ በመስቀል ላይ መሞቱን ያሰላስሉ። ይህ አስገራሚ ክስተት እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እውነተኝነት ምን ያህል ያስረዳል?
@SabbathSchool @TekalignSorato












