
በፈረንሳይ የኑሮ ውድነትን፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን እና የመንግሥት ወጪ ቅነሳን በመቃወም በበርካታ ከተሞች በተካሄደ የጎዳና ተቃውሞ ከ160 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ከ900 በላይ የፖሊስ አባላት መቁሰላቸውን ይፋዊ ዘገባዎች አመልክተዋል።
በፓሪስ ፖሊስ የአስለቃሽ ጭስ እና ግፊት ያለው ውኃ ተጠቅሟል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ፊት መሸፈኛ አድርገው ተቀጣጣይ ነገሮችን ሲወረውሩ ታይተዋል።
ከፓሪስ ውጭ ባሉ 140 ቦታዎች ጭምር የተቃውሞ ሰልፎች የተደረጉ ሲሆን እስከ እኩለ ቀን ባለው ጊዜ ከ32,800 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሏል።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ለተከሰተው ሁከትና ግጭት በዋናነት «ፅንፈኛ የግራ ክንፍ» ቡድኖችን ተጠያቂ አድርገዋል።
ባለፈው ወር በፓሪስ ሰሜናዊ ዳርቻ በሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አካባቢዎች የመምህራን እጥረትና የትምህርት ቤት መገልገያዎች መበላሸትን በመቃወም በተማሪዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ በፍጥነት በመስፋት የኑሮ ውድነትና የህዝብ አገልግሎቶች ቅሬታዎችን መሰረት አድርጎ አድጓል።
በማርሴይ፣ ሞንፔሊዬ እና ሌሎች ከተሞች የከንቲባ ቢሮና የመንግሥት ሕንፃዎች ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር የጎዳና ላይ ግጭት ውስጥ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲያን ሌኮርኑ እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ህዝቡ እንዲረጋጋጥሪ አቅርበዋል።
ሀገሪቱ የገጠማት የኢኮኖሚ ጫና እና የመንግሥት ብድር ወለድ መጠን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ፣ ሁኔታውን እ.ኤ.አ. በ2018 ከተቀሰቀሰው የ«ቢጫ ጃኬት» ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ተመሳሳይ አድርጎታል ተብሏል።
📹 AFP / CLPRESS
@TikvahethMagazine









