TIKVAH-MAGAZINE Telegram channel photo

TIKVAH-MAGAZINE

@tikvahethmagazinePublic Channel

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያና የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው። በ +251913134524 ላይ ያግኙን። ለማስታወቂያ @tikvahmagbot ላይ መረጃ ይጠይቁ።

ReligioneitalianoItalia

16.1k

Last views

193.4k (193,396 subscribers)
Membri
—
Rating
73
Total Posts
Oct 20, 2026, 2:12 PM
Aggiornato
Mar 29, 2026
Created
Stats

Stai visualizzando contenuti in italiano. Per visualizzare contenuti in un'altra lingua, cambia la lingua del sito web.

Channel Information

Channel Information
Channel NameTIKVAH-MAGAZINE
Username@tikvahethmagazine
CategoryReligione
Languageitaliano
CountryItalia
Membri193,396
Channel TypePublic Channel
Created29 mar 2026
Last Updated20 ott 2026 • 3 giorni fa
StatusActive

Classifica

Classifica globale
#118851+244
Classifica per lingua
#1239+16
Classifica per categoria
#1977+7

Crescita abbonati

Totale: 193.4K30 Days growth: +7400.4%
09/2109/2610/0110/0610/1110/1610/20
Crescita abbonati - 30 Days
DateSubscribers
21:09:2026192,656
22:09:2026192,656
23:09:2026192,656
24:09:2026192,656
25:09:2026192,653
26:09:2026192,653
27:09:2026192,653
28:09:2026192,653
29:09:2026192,653
30:09:2026192,653
01:10:2026192,653
02:10:2026192,653
03:10:2026192,653
04:10:2026192,653
05:10:2026192,653
06:10:2026192,653
07:10:2026192,653
08:10:2026192,653
09:10:2026192,653
10:10:2026192,653
11:10:2026192,653
12:10:2026193,539
13:10:2026193,539
14:10:2026193,539
15:10:2026193,539
16:10:2026193,539
17:10:2026193,539
18:10:2026193,539
19:10:2026193,539
20:10:2026193,396
Crescita abbonati - Weekly
DateSubscribers
Week of 23:03:2026193,165
Week of 30:03:2026193,117
Week of 06:04:2026192,921
Week of 13:04:2026192,873
Week of 20:04:2026192,807
Week of 27:04:2026192,807
Week of 04:05:2026192,807
Week of 11:05:2026192,701
Week of 18:05:2026192,701
Week of 25:05:2026192,701
Week of 01:06:2026192,322
Week of 08:06:2026192,322
Week of 15:06:2026192,255
Week of 22:06:2026192,390
Week of 29:06:2026192,390
Week of 06:07:2026192,390
Week of 13:07:2026192,667
Week of 20:07:2026192,600
Week of 27:07:2026192,617
Week of 03:08:2026192,617
Week of 10:08:2026192,617
Week of 17:08:2026192,939
Week of 24:08:2026192,433
Week of 31:08:2026192,603
Week of 07:09:2026192,603
Week of 14:09:2026192,656
Week of 21:09:2026192,653
Week of 28:09:2026192,653
Week of 05:10:2026192,653
Week of 12:10:2026193,539
Week of 19:10:2026193,396
Crescita abbonati - Monthly
DateSubscribers
March 2026193,148
April 2026192,807
May 2026192,701
June 2026192,390
July 2026192,600
August 2026192,433
September 2026192,653
October 2026193,396
Crescita abbonati - Yearly
DateSubscribers
2026193,396

Top 10 posts

Most viewed posts from this channel

By views
  1. #1በአንድ ዓመት - አንድ ሺ የልብ ሕሙማን ሕፃናትን የማከም መርሐግብር በጅማ ሆስፒታል ተጀመረ።43.3K
  2. #2ከሀብት አንጻር የመንግስት ትልቁ የልማት ድርጅት ነን - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል36.0K
  3. #3የዓለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካ ሲዲሲ በዩጋንዳ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ማብቃቱን አወጁ32.7K
  4. #4በሀላባ ዞን የግል ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ጊዜያዊ የነዳጅ መቅጃ ኮፖን ሳይዙ ነዳጅ መቅዳት አይችሉም ተባለ30.3K
  5. #5የፌስቡክ ባለቤት ሜታ ልጆችን ለወሲባዊ ይዝቶች በማጋለጥ 375 ሚሊየን ዶላር ተፈረደበት29.1K
  6. #6🔥 ታላቅ የቅድመ-ሽያጭ ቅናሽ — ቡልጋሪያ!28.4K
  7. #7#እንድታውቁት: የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በተፈጥሮ የከንፈርና ላንቃ ችግር ላለባቸው ህፃናትና አዋቂዎች የነፃ ቀዶ28.4K
  8. #8✅ 25% ቅናሽ!26.9K
  9. #9ትኩረት የሳበው "አርትክራፍት" ምንድን ነው ?26.7K
  10. #10"በመጪዎቹ ሳምንታት ጀምሮ ከብዙ የባለበጀት የመንግስት ተቋማት ጋር የክፍያ አማራጭ ሆነን እንመጣለን" - ኤም-26.5K

Ultimi post

TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

22 ott 2026, 02:20

Photo1/2
"ወደ 20 ሚሊዮን ብር የሚገመት የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ያለበት በመሆኑ እንዲወገድ እና ወደ መጣበት ሀገር እንዲመለስ ተደርጓል" - ዶ/ር ሰለሞን ከበደ

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በሩብ ዓመቱ ባካሄደው ጥብቅ የላብራቶሪ ምርመራ ከደረጃ በታች ሆነው ያገኛቸውን አንድ የእንስሳት መድኃኒት እና ሦስት ክትባቶች አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ማድረጉን ገለጸ።

የባለስልጣኑ የእንስሳት መድኃኒት ሬጉላተሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ እንደገለጹት፤ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ፣ ከሀገር በሚወጡ እንስሳት እና የእንስሳት ውጤቶች ላይ የጥራት እና ደህንነት የማረጋገጥ ስራ በሰፊው እየተሰራ ነው።

በእንስሳት መኖ እና መድኃኒት ላይ የጥራት ችግር እንደሚነሳ የገለጹት ዶ/ር ሰለሞን፥ አንዳንድ የሚፈለጉ መድኃኒቶች በገበያ ላይ ያለመገኘት ችግሮች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

ዶ/ር ሰለሞን ከበደ በዝርዝር ምን አሉ?

"መድኃኒቶች ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ኬላ ላይ ደህንነታቸውን በላብራቶሪ በማረጋገጥ የጥራት ችግር ያለባቸው እንዲወገዱ እያደረግን ነው።

በባለፈው ዓመት ወደ 20 ሚሊዮን ብር የሚገመት የእንስሳት መድኃኒት የጥራት ችግር ያለበት በመሆኑ ምክንያት እንዲወገድ እና ወደ መጣበት ሀገር እንዲመለስ ተደርጓል።

በተያዘው በጀት ዓመት በሩብ ዓመት ወደ 114 መድኃኒቶችን እና ክትባቶችን በመርምር አንድ መድኃኒት እና ሦስት ክትባቶች ከደረጃ በታች መሆናቸው ተረጋግጦ አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ ተደርጓል።

የእንስሳት መድኃኒትን አቅርቦት አማራጮችን ከማሻሻል አንፃር በጣም ብዙ ስራዎችን እየሰራን ነው። በገበያ ላይ በብዛት የማይገኙ መድኃኒቶችን በመመዝገብ ወደ ሀገር ውስጥ እንድገቡ እየተደረገ ነው።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አገልግሎቶቹ በመሶብ አንድ ማዕከል፣ በኢ-ሰርቪስ እና በአንድ መስኮት እየተሰጡ ነው። አሰራራችንን በዲጂታል በማድረጋችን የመድኃኒት አማራጮች እንዲኖሩ አድርጓል" ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ያለ እንስሳት ሕክምና ባለሙያ ትዕዛዝ የሚሰጡና በመድኃኒት ማዝዣ የሚታደሉ መድኃኒቶችን ለመለየት የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ በፍትሕ ሚኒስቴር መጽደቁን ጠቁመዋል።

የመድኃኒት አጠቃቀምን ለመቀነስና በሽታ እንዳይከሰት ቅድመ-መከላከል ላይ ያተኮረ የ'አንቲ ማይክሮባይል ስዋርዲሺፕ' ማኑዋል ከግብርና ሚኒስቴር እና ከፋኦ (FAO) ጋር በመሆን እየተዘጋጀ መሆኑንም አክለዋል።

ሌላው ዶ/ር ሰለሞን ያነሱት ስለ ሀገር በቀል ወይም ባህላዊ መድኃኒቶች ሲሆን በሀገራችን ከ80 እስከ 85 በመቶ የሚሆነው ጥቅም ላይ እንደሚውል ቢነገርም አሁን ላይ ወደ ገበያ መጥተው በስፋት ጥቅም ላይ እንደዋሉ አንስተዋል።

እነዚህን መድኃኒቶች በስፋት ወደ ገበያ ለማስገባት የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ አንድ የእንስሳት መድኃኒት አምራች ብቻ እንደነበር ያነሱት ዶ/ር ሰለሞን ከጊዜ ወደ ጊዜ የሀገር ውስጥ አምራቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን እና አሁን ላይ ወደ አምስት የሚደርሱ አምራቾች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
16,1000059
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

22 ott 2026, 00:47

Photo1/2
የትራምፕ አስተዳደር ከ300 ሺህ በላይ ቪዛዎችን ሰረዘ።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከጥር 2025 ጀምሮ ከ300 ሺህ በላይ የአሜሪካ ቪዛዎችን መሰረዙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ቁጥሩ ከ175 ሺህ በላይ እንደነበር ተገልጾ ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት እንዳሉት አስተዳደሩ ህግ የሚጥሱ፣ ማጭበርበር የሚፈጽሙ ወይም ብሔራዊ ደህንነትን የሚፈትኑ የውጭ ዜጎች ላይ “ምንም ትዕግስት የለንም" ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም የትራምፕን አስተዳደር ከማንኛውም ቀድሞ አስተዳደር በብዛትም ሆኖ በችኮላ ይህን መሰል ውሳኔዎችን ያሳለፈ አስተዳደር ያደርገዋል።

ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እርምጃዎችን የሕግ ባለቤትነት ሂደትን እና የሐሳብ አገላለጽ ነጻነትን ይጋፋል ሲሉ ይወቅሳሉ። በተለይም በጋዛ ጦርነት ተቃውሞ ያሰሙ እና በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳባቸውን የሰጡ ሰዎች ላይ የነበረውን ተጽእኖ አንስተው ይሞግታሉ።

ዘገባው የሮይተርስ ነው።

@TikvahethMagazine
17,7000043
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

21 ott 2026, 14:31

Photo1/2
የAI ውድድር አሁን ላይ ቀጣይነት ያለው የኃይል አቅርቦት ላይ ሆኗል ... እንዴት ?

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ውድድር ከቺፕና ከሞዴል በላይ አሁን ላይ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ተሸጋግሯል። ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መካከል ያለው ውድድር ጠንካራ የAI ሞዴል ባለቤት ከመሆን ባሻገር ያንን ሞዴል ለማስኬድ የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ኃይል በተረጋጋ ሁኔታ ማግኘት በመቻል ላይ ሆኗል።

በ2024 አራቱ ትላልቅ የአሜሪካ ኩባንያዎች (አማዞን፣ ጉግል፣ ሜታ እና ማይክሮሶፍት) 226 ቢሊዮን ዶላር አውጥተዋል። በ2025 ይህ ወደ 410 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል። በ2026 ደግሞ ወደ 725 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጡ ሲጠበቅ፥ ይህም በሁለት ዓመት ውስጥ በሦስት እጥፍ ጭማሪ ያለው ነው።

ከዚህ ኢንቨስትመንት በአብዛኛው እጅ ወደ ዳታ ሴንተሮች ይሄዳል። የዓለም አቀፍ የኢነርጂ ኤጀንሲ (IEA)፥ የዳታ ሴንተሮች የኤሌክትሪክ ፍጆታ በ2024 415 ቴራዋት-ሰዓት እንደነበርና በ2025 ወደ 485 ማደጉን ገልጿል። ጋርትነር ሪሰርች በበኩሉ ይህ በ2026 ወደ 565 ቴራዋት-ሰዓት እንደሚደርስና 26 በመቶ ጭማሪ እንደሚኖረው ይጠቁማል። ይህ ፍጆታ እስከ 2030 ድረስ ወደ 945 ቴራዋት-ሰዓት ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል።

በንጽጽር ለመመልከት ያክል፥ አንድ መደበኛ ዳታ ሴንተር የ100,000 ቤተሰቦችን ያህል ኤሌክትሪክ ይጠቀማል። አሁን እየተገነቡ ያሉ ትላልቅ ካምፖች ደግሞ ይህንን በብዙ እጥፍ የሚፈልጉ ናቸው። በፍራንክፈርት የተገነቡ ማዕከላት የአካባቢውን ኤሌክትሪክ 42 በመቶ፣ በደብሊን ደግሞ እስከ 80 በመቶ ይወስዳሉ።

በዚህ ሳቢያ በአከባቢው ለሚኖሩ ማህበረሰቦች ዘንድ ቁጣን ሲቀሰቅስ በተደጋጋሚ ተስተውሏል። በአሜሪካ ደግሞ ነዋሪዎች ተቃውሞ እስከማሰማት ደርሰዋል፤ በ2026 የመጀመሪያ አጋማሽ ቢያንስ 120 ፕሮጀክቶች ታግደዋል ወይም ዘግይተዋል።

የአፍሪካ ዳታ ሴንተሮች ማኅበር በ2026 ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ አፍሪካ ከዓለም አቀፉ አቅም 0.6 በመቶ ብቻ ትይዛለች። አሁን ያላት ንቁ አቅም 360 ሜጋዋት ሲሆን 238 ሜጋዋት በግንባታ ላይ፤ 656 ሜጋዋት ደግሞ በዕቅድ ደረጃ ተቀምጧል።

አፍሪካ ወደ 18 በመቶ የዓለም ሕዝብ ቢኖራትም ድርሻዋ በጣም ዝቅተኛ ነው። በአኅጉሪቱ ትልቁ ማዕከል በጆሃንስበርግ የሚገኘው 70 ሜጋዋት የሚጠቀመው ነው። ለአፍሪካ ትልቁ ፈተና የኃይል እጥረት ነው። ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ወደ 600 ሚሊዮን ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የላቸውም።

ውድድሩ ግን የሚቆም አይመስልም፤ የተሻለ የኃይል አቅርቦት መፍጠር በዚህ ውድድር ውስጥ ትልቅ ጉልበት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
21,3000071
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

21 ott 2026, 14:30

Photo1/2
🌅 በ1%ወርሃዊ ክፍያ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!

🌴🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ🌴🌴
የንግድ ሱቅ ከታዋቂው ቴምር ሪል እስቴት
👉ገንብተን ማስረከብ ጥያቄ አይሆንብንም ከ10 በላይ አፓርትመንት እና ሱቆችን ጥንቅቅ አርገን አስረክበናል!!
👉አሁን ደግሞ ሳር ቤት አደባባዩ ፊት ለፊት እና አፍሪካ ህብረት በ ቡልጋሪያ ላይ ሱቆችን አውጥተናል።

▪️ግራውንድ ፍሎር –10 ሜ² 3,200,000 ብር
▪️ 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 3,568,000 ብር
▪️ 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 2,625,000 ብር
▪️ 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²፡ 2,635,000 ብር
▪️ 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²፡ 2,660,000 ብር
▪️ 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²፡ 2,600,000 ብር
** አከፋፈል
👉ቅድመ ክፍያ 25%
👉ለ2 አመት ለ24 ወር በየወሩ 1%=24%
👉ስትራክቸር ሲያልቅ 10%
👉ሴራሚክ ስራ ሲያልቅ 10%
👉አልሙኒየም ስራ ሲያልቅ 10%
👉ሱቁን ሲረከቡ 21%

*100% ለሚከፍሉ የ 30% ቅናሽ
- ግራውንድ ወለል – 10 ሜ²: 2,240,000 ብር
- 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 2,497,600 ብር 
- 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 1,837,500 ብር
- 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²: 1,844,500 ብር
- 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²: 1,862,000 ብር
- 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²: 1,820,000 ብር

እንዲሁም ከተጠቀሱት ካሬ አማራጮች ውጪ ካሬ አማራጮች አሉን ይደውሉልን።
+251 98 078 2850 ቴምር ሪል እስቴት
19,0000010
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

20 ott 2026, 23:44

Photo1/2
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመሬት ይዞታ ምዝገባን ለሙያ ማህበራት የሚያስተላልፍ መመሪያ አጸደቀ

🟢 የክልሉ ካቢኔ የዲዛይን እና ቁጥጥር ባለስልጣን ማቋቋሚያ ደንብ አጽድቋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የከተሞች ህጋዊ የካዳስተር (የመሬት ይዞታ) ምዝገባ ስራን በሙያ ማህበራት ለማከናወን የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።

የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዳስታወቀው፣ መመሪያው በከተሞች የሚገኙ ይዞታዎችን ወደ ዘመናዊ የካዳስተር ስርዓት የማስገባት ሂደቱን በጥራት እና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል።

ከዚህ በተጨማሪም ካቢኔው የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ጥራት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት የሚቆጣጠር አዲስ «የዲዛይን እና ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን» የሚያቋቁም ደንብ አጽድቋል።

ቀደም ሲል በክልሉ ከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ስር ተካተው ይከናወኑ የነበሩ የህንፃ፣ የውሃ እና የመንገድ ዲዛይን እና ቁጥጥር ኃላፊነቶች ሙሉ በሙሉ ወደዚሁ አዲስ ባለስልጣን እንደሚሸጋገሩ ተገልጻል።

ምክር ቤቱ በሌሎች አጀንዳዎቹ ላይ በመምከር በክልል እና ወረዳዎች መካከል ያለውን የታክስ ስልጣን ለመወሰን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) አሰብሰብን በማሻሻል የግብር ከፋዩን ህግ ተገዥነት የሚያሳድግ የተሻሻለ ደንብ ያጸደቀ ሲሆን፤ ቀደም ሲል በቢሮ ደረጃ ተደራጅቶ የነበረውን የኮሙኒኬሽን አደረጃጀት ወደ «የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት» የሚቀይረውን ደንብም አጽድቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
21,0000030
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

20 ott 2026, 16:27

Video
#Update

በአውሮፓ ብዙ አገሮች ውስጥ የኑሮ ውድነት፣ የትምህርት ሁኔታ መበላሸት እና የመንግሥት አገልግሎቶች መዳከም ምክንያት በሆኑ ትላልቅ ተቃውሞዎች ሁከቶች ተስተውለዋል።

በተለይ በፈረንሳይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ተቃውሞዎቹ ወደ ጣሊያን፣ ቤልጂየም፣ አልባኒያ እና ሌሎች አገሮች ተዛምተዋል።

🇫🇷 ፈረንሳይ (ፓሪስ፣ ሊሞጅ፣ ማርሴይ፣ ሊዮን፣ ቦርዶ፣ ኒስ፣ ሊል)

በፈረንሳይ በበርካታ ከተሞች ተቃውሞዎች ተስተውለዋል። በእነዚህ የተቃውሞ ሰልፎች ከ550,000 እስከ 800,000 ሰዎች ተሳታፊ ሲሆኑ፥ በነበሩ ሁከቶች በዚህም ከ2,300 በላይ ሰዎች ሲታሰሩ በፓሪስ ብቻ 855 ሰዎቾ ታስረዋል። ወደ 1,000 የሚጠጉ የፖሊስና የደህንነት ሰራተኞችም ቆስለዋል።

በሊሞጅ በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደተገነባ የሚነገርለት የከተማ አዳራሽ በእሳት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። በማርሴይ፣ ሊዮን፣ ቦርዶ፣ ኒስ እና ሌሎች ከተሞች የመንግሥት ሕንፃዎችና መደብሮች ጥቃት ደርሶባቸዋል።

ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በፓሪስ እንዲሁም በሊዮን፣ ኒስ፣ ሊል፣ ማርሴይ እና ቦርዶ ጊዜያዊ የእንቅስቃሴ እገዳ ተጥሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲየን ሌኮርኑ “እገዳዎቹ ሌሊቱን ሰላም ጠብቀዋል” ብለዋል። መንግሥት “ፅንፈኛ የግራ ክንፍ” ቡድኖችን እና ወንጀለኞችን ተጠያቂ አድርጓል።

በተያያዘ በእነዚህ ህዝባዊ ተቃውሞዎች እና ሁከቶች ወቅት ከተዘረፉ የንግድ ተቋማት የተወሰዱ ንብረቶች በተለያዩ የኦንላይን መሸጫ ፕላትፎርሞች ላይ እየቀረቡ መሆኑ ተገልጿል።

🇮🇹 ጣሊያን (ሚላን፣ ቱሪን፣ ቦሎኛ)

በሚላን በተመሳሳይ ምክንያት ተቃውሞ ሲካሄድ መንግሥት ከ500 የጦር ሰራዊት አባላትን አሰማርቷል።

በተፈጠሩ ሁከቶችም ከ271 በላይ ሰዎች ሲታሰሩ አብዛኛዎቹ ወጣቶች ናቸው ተብሏል። የቅንጦት መደብሮች ብዙዎቹ ተዘግተው ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጃ ሜሎኒ አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጋቸው ተገልጿል።

🇧🇪 ቤልጂየም (ብራስልስና ሊየጅ)

በተመሳሳይ በነበሩ የተቃውሞ ሰልፎች ግጭቶች የከሰቱ ሲሆን ፖሊስ የአስለቃሽ ጭስ እና ግፊት ያለው ውሃ ለመጠቀም ተገዷል። በዚህ ምክንያትም አምስት የፖሊስ አባላት ቆስለዋል።

🇦🇱 አልባኒያ (ቲራና እና ደቡባዊ የባህር ዳርቻ ከተሞች)

በአልባኒያ “ፍላሚንጎ” ተብሎ የሚጠራው ተቃውሞ አሁንም ተባቭሶ ቀጥሏል። ተቃዋሚዎች በደቡባዊ የባህር ዳርቻ ላይ የታቀደውን ትልቅ የቱሪዝም ፕሮጀክት እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ ችግርን በመቃወም ለሳምንታት ሲታገሉ ቆይተዋል።

በቲራና እና በሌሎች ከተሞች ተቃዋሚዎች ድንጋይ፣ ተቀጣጣይ ነገሮችን እና ፍንዳታ የሚያስከትሉ ቁሶችን ሲወረውሩ ተስተውለዋል። ፖሊስ የአስለቃሽ ጭስ እና ግፊት ያለው ውሃ ለመጠቀም ተገዷል።

በነበሩ ተቃውሞዎቾ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፤ ንብረት ተጎድቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኢዲ ራማ ተቃውሞዎቹን የውጭ ሃይሎች [ኢራንና ሩሲያ] እያነሳሱት እንደሆነ ከሰዋል።

በተጨማሪ

በፖርቱጋል፣ ስፔን እና ግሪክ የኑሮ ውድነትና የቤት ችግር ላይ ተቃውሞዎች መሰማታቸው ሲገለጽ እስካሁን በእነዚህ ሀገራት የነበሩ ተቃውሞዎች አብዛኞቹ ሰላማዊ ሆነው ቀጥለዋል።

@TikvahethMagazine
22,8000093
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

20 ott 2026, 16:26

Photo1/2
🌅 በ1%ወርሃዊ ክፍያ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!

🌴🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ🌴🌴
የንግድ ሱቅ ከታዋቂው ቴምር ሪል እስቴት
👉ገንብተን ማስረከብ ጥያቄ አይሆንብንም ከ10 በላይ አፓርትመንት እና ሱቆችን ጥንቅቅ አርገን አስረክበናል!!
👉አሁን ደግሞ ሳር ቤት አደባባዩ ፊት ለፊት እና አፍሪካ ህብረት በ ቡልጋሪያ ላይ ሱቆችን አውጥተናል።

▪️ግራውንድ ፍሎር –10 ሜ² 3,200,000 ብር
▪️ 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 3,568,000 ብር
▪️ 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 2,625,000 ብር
▪️ 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²፡ 2,635,000 ብር
▪️ 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²፡ 2,660,000 ብር
▪️ 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²፡ 2,600,000 ብር
** አከፋፈል
👉ቅድመ ክፍያ 25%
👉ለ2 አመት ለ24 ወር በየወሩ 1%=24%
👉ስትራክቸር ሲያልቅ 10%
👉ሴራሚክ ስራ ሲያልቅ 10%
👉አልሙኒየም ስራ ሲያልቅ 10%
👉ሱቁን ሲረከቡ 21%

*100% ለሚከፍሉ የ 30% ቅናሽ
- ግራውንድ ወለል – 10 ሜ²: 2,240,000 ብር
- 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 2,497,600 ብር 
- 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 1,837,500 ብር
- 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²: 1,844,500 ብር
- 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²: 1,862,000 ብር
- 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²: 1,820,000 ብር

እንዲሁም ከተጠቀሱት ካሬ አማራጮች ውጪ ካሬ አማራጮች አሉን ይደውሉልን።
+251 98 078 2850 ቴምር ሪል እስቴት
19,6000019
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

20 ott 2026, 01:13

Photo1/2
ኤሎን መስክ ለሁሉም የአሜሪካ ህፃናት የስፔስኤክስ ድርሻ እንደሚሰጥ ገለጸ።

የቴስላና ስፔስኤክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሎን መስክ፣ በቀጣዩ ዓመት 2027 ለሁሉም የአሜሪካ ህፃናት አንድ የስፔስኤክስ ድርሻ እንደሚያበረክት አስታወቀ።

መስክ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ «ቀጣዩ ዓመት ለአሜሪካ ህፃናት ሁሉ አንድ የስፔስኤክስ ድርሻዬን እሰጣለሁ» ሲል አስፍሯል።

ይህ ውጥን በዩናይትድ ስቴትስ ከ18 ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸውን ግምታዊ 73 ሚሊዮን ህፃናት የሚያካትት ሲሆን፣ አሁን ባለው የኩባንያው የሼር ዋጋ (146 ዶላር ገደማ) አማካኝነት ሲሰላ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ቃል ነው የገቡት ተብሏል።

ይህ መጠን የቢሊየነሩን አጠቃላይ የተጣራ ሀብት 1 በመቶ ያህሉን እንደሚሸፍን የፋይናንስ መረጃዎች ያሳያሉ።

በተመሳሳይ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኩባንያ አንትሮፒክ ከድርጅቱ ድርሻ 5 በመቶ ለፐብሊክ ፈንድ (Public Benefit Fund) አድርጋለሁ ሲል ገልጿል።

@TikvahethMagazine
24,50000167
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

20 ott 2026, 00:47

Photo1/2
ኢትዮጵያ ለ15 ወራት ተቋርጦ የቆየውን ወደ ኳታር የስጋ ኤክስፖርት ማስጀመሯን ገለጸች።

ኢትዮጵያ ለ15 ወራት ተቋርጦ የቆየውን ወደ ኳታር የሚደረግ የስጋ ኤክስፖርት ከጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዳግም ማስጀመሯን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥልጣኑ የእንስሳት ምርት ሬጉላቶሪ መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ዶ/ር አያሌው ሹመት እንደገለጹት፣ ኳታር በኤክስፖርት መስፈርቷ ላይ ያካተተችውን ተጨማሪ ነጥብ ለማሟላት ባለመቻሉ ኤክስፖርቱ ተቋርጦ መቆየቱን ገልጸዋል።

እገዳው በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የተጣለ እንዳልነበረ ያነሱት ዶ/ር አያሌው፥ በግብርና ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት እና ከኳታር ኤምባሲዎች ጋር በተደረጉ ተከታታይ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች መፍትሔ መገኘቱን ተናግረዋል።

እንስሳቱ ከመታረዳቸው በፊት በሰበታ እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት አማካኝነት የደም ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ የጤንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲያገኙ በመደረጉ ወደ ውጭ መላክ መጀመሩን ነው ያብራሩት።

ኳታር ኢትዮጵያ ስጋ ከምትልክባቸው ሦስተኛዋ ትልቅ የገበያ መዳረሻ መሆኗን የጠቆሙት ኃላፊው፣ በቀጣይ ወደ ቻይና ገበያ ለመቀላቀል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ንግድ መረጃ ቋት መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2023 ብቻ ወደ ኳታር የላከችው የሥጋ ምርት 3.69 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኘ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
23,70000112
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

19 ott 2026, 20:19

Photo1/2
ኬንያ በጫት ጭማቂ ሕገወጥ አምራቾችን ላይ እስከ 1 ሚሊዮን ሽልንግ ቅጣት ልትጥል ነው።

የኬንያ የስታንዳርድ ቢሮ የጫት ምርትን ቀላቅለው በሚዘጋጁ መጠጦች ላይ የጥራት ማረጋገጫ ምልክትን ያላግባብ በሚጠቀሙ አምራቾች እና ነጋዴዎች ላይ ከባድ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ።

የጥራት ተቆጣጣሪው ቢሮ ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ በጫት ላይ የተመሰረቱ መጠጦች ወይም ንጥረ ነገሮች የጥራት ፈቃድ መርሃ-ግብሩ አካል እንዳልሆኑ እና ለእንደነዚህ አይነት ምርቶች ምንም ዓይነት የማረጋገጫ ፈቃድ እንዳልሰጠ አፅንኦት ሰጥቷል።

ሆኖም ጎጂ የሆኑ የጫት ንጥረ ነገሮችን የያዙ መጠጦችን ለገበያ የሚያቀርቡ አካላት፣ ለመደበኛ ፍራፍሬ ጭማቂዎች የተሰጡ ፈቃዶችን በመጠቀም ሕገወጥ አሰራር ሲከተሉ መገኘታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ይህንን የሕግ ጥሰት ሲፈጽሙ የተገኙ አካላት እስከ 1 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ወይም በእስራት እንደሚቀጡ ያስጠነቀቀው ቢሮው፣ ሸማቾች በነዚህ መጠጦች ላይ የሚደረጉ የጥራት ማረጋገጫ ጥያቄዎች ሐሰተኛ መሆናቸውን ተገንዝበው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

@TikvahethMagazine
23,5000086
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

19 ott 2026, 20:19

Photo1/2
🌅 በ1%ወርሃዊ ክፍያ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!

🌴🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ🌴🌴
የንግድ ሱቅ ከታዋቂው ቴምር ሪል እስቴት
👉ገንብተን ማስረከብ ጥያቄ አይሆንብንም ከ10 በላይ አፓርትመንት እና ሱቆችን ጥንቅቅ አርገን አስረክበናል!!
👉አሁን ደግሞ ሳር ቤት አደባባዩ ፊት ለፊት እና አፍሪካ ህብረት በ ቡልጋሪያ ላይ ሱቆችን አውጥተናል።

▪️ግራውንድ ፍሎር –10 ሜ² 3,200,000 ብር
▪️ 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 3,568,000 ብር
▪️ 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 2,625,000 ብር
▪️ 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²፡ 2,635,000 ብር
▪️ 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²፡ 2,660,000 ብር
▪️ 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²፡ 2,600,000 ብር
** አከፋፈል
👉ቅድመ ክፍያ 25%
👉ለ2 አመት ለ24 ወር በየወሩ 1%=24%
👉ስትራክቸር ሲያልቅ 10%
👉ሴራሚክ ስራ ሲያልቅ 10%
👉አልሙኒየም ስራ ሲያልቅ 10%
👉ሱቁን ሲረከቡ 21%

*100% ለሚከፍሉ የ 30% ቅናሽ
- ግራውንድ ወለል – 10 ሜ²: 2,240,000 ብር
- 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 2,497,600 ብር 
- 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 1,837,500 ብር
- 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²: 1,844,500 ብር
- 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²: 1,862,000 ብር
- 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²: 1,820,000 ብር

እንዲሁም ከተጠቀሱት ካሬ አማራጮች ውጪ ካሬ አማራጮች አሉን ይደውሉልን።
+251 98 078 2850 ቴምር ሪል እስቴት
21,5000016
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

19 ott 2026, 20:19

Photo1/4
Make.... TOYOTA
Model... Land Cruiser V8
Year... 2014 /08
Engine... V8 D4D
Drive Type... AWD
Transmission.. Manual
Status... Fulloption
pleat No ... AAL71xxx
Standard... Europe
Condition... Excellent
ከኢማባሲ ነው የወጣዉ 👈👈

Price..14,500,000 million birr Negotiable

    የማይቀርብ መኪና በፍፁም
           ፖስት አናረግም 🙏

ማንኛውም ያገለገሉ ሆነ አዲስ መኪና መሸጥ ሲፈልጉ ይደውሉልን   

  📞  0911390160
21,4000022
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

18 ott 2026, 21:40

Photo1/2
ትኩረት የሳበው "አርትክራፍት" ምንድን ነው ?

"አርትክራፍት" በሚል መጠሪያ የመጣውና እንደ ፎቶሾፕ፣ ፕሪሚየር ፕሮ እና አክሮባት ያሉ ታዋቂ የአዶቤ ክሬቲቭ ክላውድ መተግበሪያዎችን በነጻ የሚያቀርበው የሶፍቶዌር ልማት ከሰሞኑ ከቴክኖሎጂው መንደር መነጋገሪያ የሆነ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል።

ፕሮጀክቱ በሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) አማካኝነት ኮድ የማስጻፍ አሰራርን (Vibe Coding) በመጠቀም የተገነባ በመሆኑ፣ የሶፍትዌር ልማት ኢንዱስትሪን አቅጣጫ ሊለውጥ የሚችል ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ተወስዷል።

ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደ አዶቤ እና ማይክሮሶፍት ያሉ ምርቶቻቸውን በከፍተኛ የደንበኝነት ክፍያ እና የውል ማቋረጫ ቅጣት ምክንያት ያለባቸውን ቅሬታዎች መነሻነት የተጀመረ እንደሆነ ተነግሯል።

በአንትሮፒክ የተሰራውን የClaude Opus 5.5 ሞዴል በመጠቀም እና በራስት (Rust) ፕሮግራሚንግ ቋንቋ የተገነባው ይህ ስብስብ፤ ፎቶክራፍት (Photoshop)፣ ፊልምክራፍት (Premiere Pro)፣ ላይትክራፍት (Lightroom) እና ፒዲኤፍክራፍት (Acrobat) የመሳሰሉ መተግበሪያዎችን ያካተተ ነው።

ፕሮጀክቱ ልዩ ትኩረት እንዲያገኝና አስገራሚ ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የኮዲንግ ቋንቋን ተጠቅሞ ከማበልጸግ ይልቅ፣ የተፈጥሮ ቋንቋ ትዕዛዞችን በመጠቀምና ውጤቱን በመገምገም የተገነባ መሆኑ ነው።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት እንደሚሞከሩት ለማስመሰል ብቻ ሳይሆን ትልልቆቹ ሶፍትዌሮች የሚሰሩትን ሥራዎች በጥራት ማከናወኑና ያለምንም ክፍያ በነጻ መቅረቡ ነው።

ይህ አሰራር ከዚህ ቀደም ለወራት ወይም ለዓመታት የፈጀ እና ትልቅ የሰው ሃይል ይጠይቅ የነበረ የሶፍትዌር ልማት ሂደት፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊከናወን እንደሚችል ማሳያ ሆኗል።

አርትክራፍት የሶፍትዌር ኢንዱስትሪውን ተደራሽነት በማስፋት እና የውድ የደንበኝነት ዋጋዎችን በመፈታተን ረገድ አዲስ አቅጣጫ ማስቀመጡን የዘርፉ ተመራማሪዎች ይስማሙበታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
26,70000143
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

18 ott 2026, 21:39

Photo1/2
🌅 በ1%ወርሃዊ ክፍያ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!

🌴🌴ቴምር ፕሮፐርቲስ🌴🌴
የንግድ ሱቅ ከታዋቂው ቴምር ሪል እስቴት
👉ገንብተን ማስረከብ ጥያቄ አይሆንብንም ከ10 በላይ አፓርትመንት እና ሱቆችን ጥንቅቅ አርገን አስረክበናል!!
👉አሁን ደግሞ ሳር ቤት አደባባዩ ፊት ለፊት እና አፍሪካ ህብረት በ ቡልጋሪያ ላይ ሱቆችን አውጥተናል።

▪️ግራውንድ ፍሎር –10 ሜ² 3,200,000 ብር
▪️ 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 3,568,000 ብር
▪️ 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²፡ 2,625,000 ብር
▪️ 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²፡ 2,635,000 ብር
▪️ 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²፡ 2,660,000 ብር
▪️ 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²፡ 2,600,000 ብር
** አከፋፈል
👉ቅድመ ክፍያ 25%
👉ለ2 አመት ለ24 ወር በየወሩ 1%=24%
👉ስትራክቸር ሲያልቅ 10%
👉ሴራሚክ ስራ ሲያልቅ 10%
👉አልሙኒየም ስራ ሲያልቅ 10%
👉ሱቁን ሲረከቡ 21%

*100% ለሚከፍሉ የ 30% ቅናሽ
- ግራውንድ ወለል – 10 ሜ²: 2,240,000 ብር
- 1ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 2,497,600 ብር 
- 2ኛ ፎቅ – 12 ሜ²: 1,837,500 ብር
- 3ኛ ፎቅ – 13 ሜ²: 1,844,500 ብር
- 4ኛ ፎቅ – 16 ሜ²: 1,862,000 ብር
- 5ኛ ፎቅ – 17 ሜ²: 1,820,000 ብር

እንዲሁም ከተጠቀሱት ካሬ አማራጮች ውጪ ካሬ አማራጮች አሉን ይደውሉልን።
+251 98 078 2850 ቴምር ሪል እስቴት
23,7000015
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 19:19

Photo
በፈረንሳይ በተደረገ ተቃውሞ ከ160 በላይ ሰዎች ሲታሰሩ፤ ከ900 በላይ ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በፈረንሳይ የኑሮ ውድነትን፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን እና የመንግሥት ወጪ ቅነሳን በመቃወም በበርካታ ከተሞች በተካሄደ የጎዳና ተቃውሞ ከ160 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ከ900 በላይ የፖሊስ አባላት መቁሰላቸውን ይፋዊ ዘገባዎች አመልክተዋል።

በፓሪስ ፖሊስ የአስለቃሽ ጭስ እና ግፊት ያለው ውኃ ተጠቅሟል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ፊት መሸፈኛ አድርገው ተቀጣጣይ ነገሮችን ሲወረውሩ ታይተዋል።

ከፓሪስ ውጭ ባሉ 140 ቦታዎች ጭምር  የተቃውሞ ሰልፎች የተደረጉ ሲሆን እስከ እኩለ ቀን ባለው ጊዜ ከ32,800 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል ተብሏል።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት ለተከሰተው ሁከትና ግጭት በዋናነት «ፅንፈኛ የግራ ክንፍ» ቡድኖችን ተጠያቂ አድርገዋል።

ባለፈው ወር በፓሪስ ሰሜናዊ ዳርቻ በሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አካባቢዎች የመምህራን እጥረትና የትምህርት ቤት መገልገያዎች መበላሸትን በመቃወም በተማሪዎች የተጀመረው እንቅስቃሴ በፍጥነት በመስፋት የኑሮ ውድነትና የህዝብ አገልግሎቶች ቅሬታዎችን መሰረት አድርጎ አድጓል።

በማርሴይ፣ ሞንፔሊዬ እና ሌሎች ከተሞች የከንቲባ ቢሮና የመንግሥት ሕንፃዎች ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር የጎዳና ላይ ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲያን ሌኮርኑ እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ህዝቡ እንዲረጋጋጥሪ አቅርበዋል።

ሀገሪቱ የገጠማት የኢኮኖሚ ጫና እና የመንግሥት ብድር ወለድ መጠን ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ፣ ሁኔታውን እ.ኤ.አ. በ2018 ከተቀሰቀሰው የ«ቢጫ ጃኬት» ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ተመሳሳይ አድርጎታል ተብሏል።

📹 AFP / CLPRESS

@TikvahethMagazine
13,4000081
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 19:18

Photo
ፕራይም ሪል እስቴት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እና የቦሌ ሜጋ ሳይት ሽያጭ ይፋ አደረገ!

​የእርስዎስ የቤት ባለቤት የመሆን ህልም መቼ ነው የሚሳካው?

የኖር ሸገር እና የሴንትራል ፕሮፐርቲስ እህት ኩባንያ ፕራይም ሪል እስቴት በቅርብ ቀናት በሚመረቁ እና በአዲስ መልክ በተጀመሩ ሳይቶቹ ላይ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ጥሪ አቀረበ።

​ኩባንያው የቦሌ ሚሊኒየም ፕላዛ አፓርትመንት ፕሮጀክት ምረቃን ባከናወነበት መርሃ-ግብር ላይ የቦሌ ሜጋ ሳይቱን በይፋ ለሽያጭ አቅርቧል።

ይህ ስኬት ለቀጣይ ፕሮጀክቶችም በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኙት እንደ ኖር ሸገር እና ሴንትራል ፕሮፐርቲስ ላሉ እህት ኩባንያዎች መነሻ በመሆን በተመሳሳይ ፍጥነት፣ ጥራትና ታማኝነት ተገንብተው እንደሚጠናቀቁ ታውቋል።

​ለበለጠ መረጃና ለቀጣይ ሳይቶች ምዝገባ፦
​ስልክ፦ +251 940777766
​ዌብሳይት፦ Primerealestateplc.com
​አድራሻ፦ ሸዋ ዳቦ ጎን ከጌቱ ኮሜርሻል ፊት ለፊት

#ቃልን_በተግባር!
12,3000012
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 17:20

Photo
የግብፁ ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ የስልጣን ዘመናቸው በ2030 እንደሚያበቃ ገለጹ።

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ የስልጣን ዘመናቸው እ.ኤ.አ. በ2030 እንደሚያበቃ እና ከስልጣን የመልቀቃቸው ጉዳይ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ እንደሚሆን ይፋ አደረጉ።

የ71 ዓመቱ አል-ሲሲ በግብፅ ወታደራዊ አካዳሚ በተካሄደ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የሀገሪቱ ህገ-መንግስት እንደማይነካ እና የስልጣን ዘመናቸው ማብቃት ለውይይት የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

እ.ኤ.አ. በጁላይ 2013 የተከሰተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተንተርሶ በሥልጣን ላይ የነበሩትን የግብፅ ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ሙርሲን ከስልጣን በማውረድ በሰኔ 2014 በይፋ ቃለ-መሃላ ፈጽመው ወደ ሥልጣን የመጡት አል-ሲሲ፣ እስካሁን በሦስት ምርጫዎችን አሸንፈዋል።

የቀድሞው ጦር አዛዥ የነበሩት ፕረዚዳንቱ፥ በመጀመሪያው ዙር ለ4 ዓመታት የመሩ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2019 በተደረገው ህገ-መንግስታዊ ህዝበ-ውሳኔ የፕሬዝዳንታዊ ዘመኑ ከ4 ወደ 6 ዓመታት በመራዘሙ ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ዙር ለስድስት ዓመታት ግብጽን የመምራት ዕድል አግኝተዋል።

በዚህም መሠረት እስካሁን ለ12 ዓመታት ከ4 ወራት ገደማ በስልጣን ላይ የቆዩት አል-ሲሲ፣ በ2030 የስልጣን ዘመናቸው ሲያበቃ በአጠቃላይ ለ16 ዓመታት ግብፅን መርተው የሚያበቁ ይሆናል።

@TikvahethMagazine
15,8000099
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 13:48

Photo
"ካልታሰበ የድንገተኛ ወጪ ራስን እና ቤተሰባችሁን ለመጠበቅ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል ሁኑ" - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ #በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የነባር እና የአዲስ አባላት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።

የጤና መድህን አባልነት ምዝገባው እስከ #ህዳር_30_2019 ዓ.ም እንደሚቆይ የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ ገልጸዋል።

በዚህ የነባር እና የአዲስ አባላት ምዝገባ በመደበኛ የስራ መስክ የተሰማሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ያላቸው ዜጎች መመዝገብ ይችላሉ።

ቢሮው በሰጠው መግለጫ፥ ዜጎች አባልነታቸውን ለማሳደስ ሲመጡ የጤና መድህን ደብተራቸውን መያዝ አለባቸው ያሉ ሲሆን አዲስ ተመዝጋቢዎች ደግሞ  የነዋሪነት መታወቂያቸውን መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ በመግለጫው፥ ከ2.75 ሚሊየን በላይ ዜጎች በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል መሆናቸውን አንስተው በተያዘው በጀት ዓመት የአባልነት ቁጥሩን በ10 በመቶ በማሳደግ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን አባል ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንን ተናግረዋል። 

በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ 3.2 ሚሊየን በላይ የጤና መድህን አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በ 2018 ዓ.ም ለማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት አመታዊ መዋጮ የ1.3 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን እና ለጤና አገልግሎት ክፍያ ለጤና ተቋማቶች 2 ቢሊየን ብር በላይ መከፈሉ ተጠቁሟል።

ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ አክለውም በ 2019 ዓ.ም የከተማ አስተዳደሩ ለዚሁ ተግባራት የሚውል 2.3 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን ጠቁመዋል።

በዚህም ከ892 ሺህ በላይ የድሃ ድሃ ወይም ምንም አይነት የመክፈል አቅም የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ዓመታዊ መዋጮ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን አስረድተዋል።

በተጨማሪም፥ "ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰብ አባላት ከዚህ ቀደም የነበረውን አተገባበር በማስቀጠል የመሰረታዊ ቤተሰቡን 50 በመቶ  መዋጮ ይከፍላሉ" ብለዋል።

አዲስ ተመዝጋቢዎችም ሆኑ ነባር አባላት በገቢ እርከናቸው ደረጃ መሰረት የክፍያ መጠናቸው ከፍተኛ 10,500 ብር፣ መካከለኛ 2,500 ብር፣ ዝቅተኛ የሆኑ ደግሞ 1,500 ብር መክፈል እንዲከፍሉ ተቀምጧል።

በከተማዋ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የተቀመጠውን መዋጮ በመክፈል ዓመቱን ሙሉ በሁሉም የመንግስት የጤና ተቋማቶች አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ ይሆናል።

ነዋሪው እራሱን እና ቤተሰቡን ካልታሰበ የድንገተኛ ወጪ ለመጠበቅ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል እንዲሆን ቢሮ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ላይ ጥሪ አቅርቧል።

የመጨረሻው የመክፈያ ቀናቶች ላይ ብዙ ጊዜ የወረፋ መጨናነቆች እና ሰልፎች ስለሚኖሩ ማኅበረሰቡ ይህን ተረድቶ ዛሬ ነገ ሳይል መክፈል እንዳለበትም አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
17,6000051
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 13:35

Photo
የአፍሪካ ሲዲሲ በኮንጎ ለኢቦላ ወረርሽኝ የተመደበ ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ መጥፋቱን አመለከተ።

የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ACDC) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለኢቦላ ወረርሽኝ ምላሽ የተመደበ ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ገንዘብ የት እንደደረሰ ባለመታወቁ ጥብቅ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠየቀ።

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ በኪንሻሳ በሰጡት መግለጫ፣ ለጋሾች 962 ሚሊዮን ዶላር ለአስፈፃሚ አጋር አካላት መለቀቁን ቢገልጹም፣ ከኮንጎ ጤና ባለሥልጣናት ጋር በተደረገ የጋራ ማጣራት መሬት ላይ የዋለው ከ230 ሚሊዮን ዶላር ያልበለጠ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዚህም ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነው የገንዘብ መጠን የገባበት አለመታወቁን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የጠቆሙት።

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው ስብሰባ ላይም ገንዘቡን ከተቀበሉ አጋር አካላት መካከልም ከ30 በመቶ ያነሱት ብቻ የገንዘብ አጠቃቀማቸውን ለማስረዳት መቅረባቸውን ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ሪፖርት በማያቀርቡ አካላት በኮንጎ እንዳይሠሩ መታገድን ጨምሮ፣ በመላው አፍሪካም ጥቁር መዝገብ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ/ም

@TikvahethMagazine
15,0000068
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 13:35

Photo
ሀገራዊና አለማቀፋዊ እድሎችን ዩዝ ቱዩዝን ተቀላቅለው ይከታተሉ። በቻናሉ የየትምህርት ፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና መድረኮች፣ የስራ፣ የስልጠና፣ የበጎ ፍቃድ ስራ እንዲሁም ሌሎች ዕድሎችም ይቀርቡበታል፡፡

ቴሌግራም ቻናል ይጫኑ 👉🏼 @y2123
እኛ ሌሎችን ከፍ በማድረግ እንነሳለን !
12,500000
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 13:30

Photo
የዲፕሎማት መንደር ብስራተገብርኤል

🔥 አማን ፕሮፐረቲስ ብስራተ ገብርኤል ሁለተኛ ሳይት ከኦልማርት ሱፐርማርኬት ፊትለፊት
! 🏠
💥70% ብቻ ከፍለው 30% ቅናሽ የተደረገባቸውን ቤቶች አልያም በካሬ 115ሺ ብር በ 15% ቅድመ ክፍያ! ✨

💥 ልዩ ልዩ  የክፍያ አማራጮች
✅ 70% ብቻ ይክፈሉ፤ 30% ቅናሽ ያግኙ!
✅ 15% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን 85% በ2 ዓመት ከ6ወር በ9 ዙር የግንባታ ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ይክፈሉ።


🏠 82 ካሬ – ባለ1 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 6.6 ብር ሚሊዮን 70%
30% - 2.8 ሚሊየን ብር 30% ቅናሽ

🏠 110 ካሬ – ባለ2 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 12.6ሚሊዮን ብር
30% - 3.7 ሚሊዮን ብር ቅናሽ

🏠 163 ካሬ – ባለ3 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 13.1ሚሊዮን ብር
30% - 5.6ሚሊየን ብር ቅናሽ

📞 ለበለጠ መረጃ +251972767112
14,300008
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 02:22

Photo
ከተሾመች ከ5 ቀን በኋላ ከሥልጣን የተነሳችው የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬተሪያት

በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተሾማ የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬተሪ በመሆን የተቀጠረችው ኬቲ ዘካሪያ በኃላፊነቷ በቆየች በአምስት ቀናት ውስጥ ከቦታዋ መነሳቷ ተነግሯል።

ዘካሪያ ከኃላፊነቷ እንድትነሳ ከተደረገባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል የመጀመሪያው የመገናኛ ብዙኃን መግለጫዋ ላይ የደረሰባት ነቀፉ ዋነኛው ነው ተብሏል።

ለ14 ደቂቃዎች ብቻ በቆየው በዚህ መግለጫ አብዛኛውን ጊዜ የተጻፈ መግለጫ ስታነብ የነበረ ሲሆን፣ በዕለቱ ጥያቄ የፈቀደችውም ለሦስት ወግ አጥባቂ የዜና ተቋማት ብቻ በመሆኑ ከፍተኛ ትችት አስተናግዳለች።

በተጨማሪም "ጠበቃ" እንደሆነች ቢነገርም የሕግ ትምህርት መውጫ ፈተናን (Bar Exam) እንዳላለፈች መጋለጡ ከመግለጫው በተጨማሪ የሙያ ብቃት ጥያቄ እንዲነሳባት ሆኗል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት፣ ዘካሪያ በመገናኛ ብዙኃን በኩል ከባድ አቀባበል እንደገጠማት ገልጸው፣ ሥራውን እንደገና እንድታስብበት መምከራቸውን ገልጸዋል።

ይህም በዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬተሪነት ታሪክ አጭሩ የስልጣን ጊዜ ያደርገዋል። ዘካሪያ ወደ ሌላ የካቢኔ የሥራ ቦታ ልትዛወር እንደምትችል ቢገለጽም ከዋይት ሀውስ በኩል እስካሁን የተሰጠ ማረጋገጫ የለም።

@TikvahethMagazine
20,40000126
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

17 ott 2026, 01:38

Photo
ንብረታቸው በማስፈራራት እየወሰደ ያስቸገረ ልጃቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ካጋለጡት በኋላ በቁጥጥር ሥር ዋለ።

ወላጅ እናቱን በተደጋጋሚ በማስፈራራትና በዛቻ ወንጀል በመፈጸም፣ እንዲሁም ንብረቶቿን ያለፈቃዷ በመውሰድና በመሸጥ ለግል ጥቅሙ ሲያውል ነበር የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ማራናታ ቢተው የተባለ ግለሰብ በድሬዳዋ ከተማ በፓሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው እናቱ ጉዳዩን በግል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በማጋራት ለሕዝብ ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው።

ከዚህ ቀደም ግለሰቡ ወላጅ እናቱን በማስፈራራትና ዛቻ ወንጀል በመፈጸም ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ለፍርድ ቤት መቅረቡን የፓሊስ መረጃ ያሳያል።

በወቅቱ የግል ተበዳይ የሆኑት ወላጅ እናቱ ይቅርታ እንዲደረግለት ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ ግለሰቡ (15,000) አስራ አምስ ሺህ የብር ቅጣት እና በሁለት አመት ገደብ ከእስር ተለቆ ነበር።

ሆኖም ግለሰቡ ከዚህ በፊት በተፈጸመው ድርጊት ሳይታረም እንደገና እናቱን በማስፈራራትና ንብረቶቿን በግዴታ በመውሰድ ለግል ጥቅሙ አውሏል በሚል ዳግም ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ታዲያ እናት ጉዳዩን በማኅበራዊ ሚዲያቸው ማጋራታቸውን ተከትሎ ድሬዳዋ ፖሊስም በጉዳዩ ላይ ባደረገው ጥብቅ ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

መረጃው የድሬዳዋ ፓሊስ ነው።

@TikvahethMagazine
21,10000116
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

Photo
የአሜሪካ ዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ የሚከፍተው ቢሮ ነገ ስራ ይጀምራል።

በአዲስ አበባ በሚከፈተው እና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የፍልሰት ጉዳዮች ለማስተናገድ የተቋቋመው የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት ቢሮ በነገው ዕለት ስራ ሊጀምር ነው።

በዚህ ቢሮ ለመስተናገድ የሚሹ ኢትዮጵያውያን አስቀድመው ቀጠሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አገልግሎቱ የገለጸ ሲሆን፣ ቢሮው ለቪዛ ማመልከቻዎች ውሳኔ የሚሰጥ እንዳልሆነም አስታውቋል።

ሆኖም ቢሮው ኢትዮጵያውያን ለፍልሰት ማመልከቻዎቻቸው የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራን ያከናውናል። የተጠረጠሩ የሰነድ ማጭበርበሮችን የሚመረምሩት እና የቤተሰቦችን ዝምድና ለማረጋገጥ የዘረ-መል ናሙናዎችን የሚሰበስቡት በአዲስ አበባ የሚከፈተው የአገልግሎቱ ቢሮ ሰራተኞች ይሆናሉ። እነዚህ ስራዎች ከዚህ ቀደም ሲከናወኑ የነበረው ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ነበር።

የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት ወሳኝ የስራ ኃላፊነቶች ያላቸውን እነዚህን ተግባራት አዲሱ ቢሮ በቀጥታ ለማከናወን የሚያስችለውን ልዩ ውክልና ይሰጠዋል። ከዩናይትድ ስቴትስ ውጪ 11 ተመሳሳይ ቢሮዎች ያሉት አገልግሎቱ፣ በአዲስ አበባ የሚከፍተው ቢሮ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ የሚገኘውን በመከተል በአፍሪካ ሁለተኛው ይሆናል።

በናይሮቢ የሚገኘው ቢሮ በዩናይትድ ስቴትስ ሕጋዊ ፈቃድ የተሰጣቸው ግለሰቦችና ስደተኞች ዘመዶቻቸውን ለመውሰድ የሚያስችለውን ማመልከቻዎች ተቀብሎ ያስተናግዳል።

በአሜሪካ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ከአገሪቱ ወጥተው ተመልሶ የመግባት ፈቃድ ቢያስፈልጋቸው ማመልከቻ የሚያቀርቡት በኬንያ ለሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ በዚሁ ቢሮ በኩል ነው።

ቢሮው ለመሰል ማመልከቻዎች ውሳኔ ባይሰጥም እያረጋገጠ ለኤምባሲው ያስተላልፋል። ዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ውክልና የሚሰጠውን ቢሮ በኢትዮጵያ ለመክፈት የወሰነችው፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአፍሪካ የቪዛ አገልግሎት በተመረጡ ቀጠናዊ ማዕከላት ብቻ እንዲከናወን ማድረጉን ተከትሎ ነው።

ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ይህ ውሳኔ፣ የአሜሪካ የቪዛ አገልግሎት አሰጣጥ ጥብቅ የደህንነት ፍተሻና ምርመራ መስፈርቶች እንዲኖሩትና ሃብቶችና የአሰራር አቅምን ከአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ጋር እንዲጣጣም የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

በውሳኔው መሰረት በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚገኘውን ጨምሮ በ25 የተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች ከነሐሴ 26 ቀን 2018 ጀምሮ የቪዛ አገልግሎት መስጠት አቋርጠዋል።

የኢትዮጵያ ጎረቤቶች በሆኑት በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎችም መደበኛ የቪዛ አገልግሎት ማቋረጣቸው ይፋ ተደርጓል።

በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከፍልሰት ውጪ ለሆኑ ለጉብኝት፣ ለስራ እና ለትምህርት ጉዞ ወደ አሜሪካ መግባት የሚሹ ኤርትራውያን የቪዛ ማመልከቻዎቻቸውን ማቅረብ የሚጠበቅባቸው በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ለሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ እንደሆነ አሳውቋል። ለፍልሰት ቪዛ የሚያመለክቱ ኤርትራውያንን የሚቀበለው ግን በኬንያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።

ይህ ዘገባ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።
21,6000066
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

Photo
🌼 አዲስ አመት እየደረሰ ነው!!!!!  ታዲያ ለወዳጅ ዘመድዎ ምን አይነት ስጦታ ለመስጠት አስበዋል??

🌟 በ2019 ዓ.ም ለሚወዱት ሰው ፣ ፍቅረኛ ፣ ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ትርጉም ያለው ስጦታ ይፈልጋሉ?

" BMK Crafts ፣ መልሰው የማያገኙትን ውድ ጊዜ ወደ የማይረሱ ትውስታዎች ይለውጥሎታል! "

🫰 የምናቀርበው፡-

☑️ Custom Acrylic Portrait Lamps

☑️ Handmade Gift Boxes with Flowers & Photos

☑️ Personalized Letters & Frames

☑️ Birthday, Anniversary, Graduation & More!

🚚 በአዲስ አበባ ላላችሁ 22 ጎላጎል ህንፃ ጀርባ ፤ አቢሲንያ ሽሮ ፊት ለፊት ፤ 22 ፕላስ የገበያ ማዕከል በሚገኘው ሱቃችን በመምጣት ፤ ካልሆነም ደግሞ ወደ አላችሁበት በሞተረኛ እንልክላችኋለን!

📌 ክ/ሀገር ላላችሁም ወደ አላችሁበት ድረስ እንልካለን።

የምትወዷቸውን ሰዎች ክብር እና ልዩ የሆነ ስሜት እንዲሰማቸው ያድርጉ።

✉️ ለማስራት አሁኑኑ መልእክት ይላኩልን።
 📞 0915560799 / https://t.me/BMSolo99
 📱 ቴሌግራም ቻናል:  https://t.me/bmkcrafts
 📱  የጂጂ ገበያ ማስፈንጠሪያ: https://jiji.com.et/shop/bmk-shopping
17,3000013
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

Photo
“ቤት ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋል” ብለው እያሰቡ ነው?🤔

🔥 ቴምር ሪል እስቴት | መገናኛ ዲያስፓራ አደባባይ ፊት ለፊት ላይ አዲስ ዕድል! 🏠
💥40% ብቻ ከፍለው 60% ቤቱን ሲረከቡ እንዲከፍሉ እኛ አመቻችተንልዎታል! ✨

💥 ልዩ ልዩ  የክፍያ አማራጮች
✅ 40% ብቻ ይክፈሉ፤ 10% ቅናሽ ያግኙ! ቀሪውን 60% ቤትዎን ከተረከቡ በኋላ መክፈል ይችላሉ
✅ 20% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን 80% በ3 ዓመት የግንባታ ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ይክፈሉ።
✅ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ አለን

🏠 60 ካሬ – ባለ1 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 7,500,000 ብር
20% - 1.5 ሚሊየን
40% - 3 ሚሊየን
100% ከከፈሉ - 4,875,000 ብር

🏠 90 ካሬ – ባለ2 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 11,250,000 ብር
20% - 2.2 ሚሊየን
40% - 4.5 ሚሊየን
100% ከከፈሉ ፦ 7,312,500 ብር

🏠 112 ካሬ – ባለ3 መኝታ
ጠቅላላ ዋጋ - 14,000,000 ብር
20% - 2.8 ሚሊየን
40% - 5.6 ሚሊየን
100% ከከፈሉ ፦ 9,100,000 ብር

📞 ለበለጠ መረጃ +251 980 782 850
ቴምር ሪል እስቴት ለደንበኞቹ ታማኝ
13,7000011
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

Photo
🔥የከተማችን ታላቁ የንግድ ማዕከል መርካቶ ተክለሐይማኖት መገኛቸውን ያረጉ በልዩነት ቅናሽ የተደረገባቸው የንግድ ሱቆች ይዘንላቹ መጥተናል!

👉በ 11 ፣ 16 ፣ 22 እና 32 ካ.ሜ አማራጭ ሲሆኑ

💰የዋጋ መነሻቸውም:-
👉ግራወንድ ላይ
ሙሉ ክፍያ : 4,950,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 1,495,000 ብር

👉1ኛ ወለል
ሙሉ ክፍያ : 4,400,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 1,320,000 ብር

👉2ተኛ ወለል
ሙሉ ክፍያ : 3,795,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 1,138,500 ብር

👉3ተኛ ወለል
ሙሉ ክፍያ : 3,300,000 ብር
ቅድመ ክፍያ : 990,000 ብር

የሚያኙት ጥቅሞች:-
👉 በተጣራ ካ.ሜ (Net Area) ብቻ የሚሸጡ መሆናቸው
👉በ 4ቱም አቅጣጫ የመንገድ አማራጮች መኖሩ
👉 መረከቢያ ጊዜ 1 ዓመት መሆኑ
👉እስከ 15% የሚደርሱ ልዩ ቅናሾች ያገኛሉ

🔥ማሳሰብያ : ይህ ዋጋ የሚያገለግለው ቀድመው ለመጡ 20 ደምበኞች ብቻ ሲሆን ለበለጠ መረጃ እና ለሳይት ጉብኝት በ 0906926956 ይደውሉልን!
ቴሌግራም:- https://t.me/Realeastateaddis
17,2000013
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

Photo
በአንድ ዓመት - አንድ ሺ የልብ ሕሙማን ሕፃናትን የማከም መርሐግብር በጅማ ሆስፒታል ተጀመረ።

ኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ በአንድ ዓመት ለአንድ ሺህ የልብ ሕሙማን ሕፃናት ነፃ ሕክምና የመስጠት መርሐግብር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ለ 50 ሕፃናት ሕክምና በመስጠት በይፋ መጀመሩን አበሰረ።

ከጣልያን ሀገር የመጡ የሕክምና ባለሙያዎች ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ለማከናወን ቅዳሜ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም ጠዋት ጅማ ከተማ ሲደርሱ የሆስፒታሉ ማህበረሰብ፣ አባገዳዎች፣ ሀደስንቄዎችን ጨምሮ የጅማ ከተማ ሕዝብ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

የሕክምና ቡድኑ ወዲያውኑ ወደሥራ በመግባት ሥራውን የጀመረ ሲኾን በቀጣይ ስምንት ቀናት ለ50 ሕፃናት ሕክምናውን እንደሚሰጥ አቶ ብርሃን ተድላ የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ ገልፀዋል።

መርሐግብሩ በ 2019 ዓ.ም ዓመቱን ሙሉ በ10 የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከሚገኙ የመንግስት ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር የሚቀጥል መሆኑን አቶ ብርሃን ጠቅሰው በአንድ ዓመት ጊዜ 1 ሺህ ሕፃናት ሕክምናውን ለማድረስ እንደሚሰራ አብስረዋል።

የመርሐግብሩ ዓላማ በተመለከተ ሲያብራሩም በትራንስፖርት ችግርና በአቅም ማነስ ምክንያት ሕክምና ማግኘች ያልቻሉ የልብ ሕሙማን ሕፃናት ባሉበት በመድረስ ሕክምናውን መስጠት እንዲሁም የሆስፒታሎችንና የዘርፉ ባለሙያዎች አቅም እንዲያድግ በማገዝ በቀጣይ ሥራውን ራሳቸውን ችለው እንዲያከናውኑ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑ ጠቁመዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚደንት ጨምሮ የሆስፒታሉ ከፍተኛ ሥራ መሪዎች ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት አምባሳደር ፍፁም አረጋ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት የኸርት ቱ ኸርት ግብረሠናይ ድርጅት መሥራች አቶ ብርሃን ተድላ እና በሳቸው ግብዣ ከጣልያን ሀገር የመጡ የሕክምና ባለሙያዎች ለ1000 የልብ ሕሙማን ሕፃናት ነፃ ቀዶ ሕክምና ለመስጠት የታቀደውን ሰፊ መርሐግብር በዛሬው ዕለት በጅማ ሆስፒታል ለ50 ሕፃናት ሕክምና መስጠት የመጀመሪያውን መርሐግብር አስጀምረዋል።

ይህን መርሐግብር አቅም ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖች፣ የዳያስፖራ ማኀበረሰብ አካላት በተጨማሪ እያንዳንዱ ዜጋ የማኪያቶ ወጪውን ጭምር በመለገስ ማገዝ እንዳለበት አሳስበዋል።

ለዚህ ታላቅ መርሐግብር ስኬት ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ጨምሮ ከጣልያን ሀገር የመጡ ባለሙያዎች እንዲሁም የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታልን አመራርና ባለሙያዎችን አመስግነዋል።

ይህ መልዕክት በኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድየቀረበ ነው።
43,30000242
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

ከሀብት አንጻር የመንግስት ትልቁ የልማት ድርጅት ነን - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 900 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና ወደ 1 ትሪሊዮን ብር እየተጠጋ እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ከሀብት መጠኑ አንጻር የመንግስት ትልቁ የልማት ድርጅት መሆኑን ገልጿል።

• ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 124.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የቻለ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ 39.55 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ በማስመዝገብ ከኪሳራ ወጥቶ ወደ ትርፋማነት ተሸጋግሯል።

• በበጀት ዓመቱ ለጎረቤት ሀገራት ከተደረገ የኃይል ኤክስፖርት እና ከዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች ሽያጭ 475.77 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ እድገት አሳይቷል።

• በበጀት ዓመቱ ከተመረተው ጠቅላላ የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 52 በመቶ የሚሆነው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገኘ ሲሆን፣ ግድቡ ሙሉ በሙሉ ወደ ኦፕሬሽን መግባቱ ለተቋሙ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል።

• በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ 21 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ያሏት ሲሆን፣ ጠቅላላ የተተከለው የማመንጨት አቅም 9,730 ሜጋ ዋት መድረሱ ተጠቅሷል።

• ተቋሙ ከ20 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው የማስተላለፊያ መስመሮች እና 170 የማከፋፈያ ጣቢያዎችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ 7,726 ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉትና ከእነሱም 18 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን አስታውቋል።

• ከተፈቀደው 152 ቢሊዮን ብር የበጀት አጠቃቀም ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው በተቋሙ በራሱ የውስጥ ገቢ የተሸፈነ ሲሆን፣ ይህም ቀደም ሲል ይደረግ የነበረውን የባንክ ብድር ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ ቀልሶታል።

📷የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የ 2018 በጀት አመት ክንውን ሪፖርት እና የ 2019 በጀት ዓመት ዋና ዋና እቅዶችን አስመልክቶ ዋና አስፈጻሚው ኢ/ር አሸብር ባልቻየሰጡትን መግለጫ ያድምጡ 👉  https://youtu.be/CUSOQRy_Iow?si=ZxwWYO58k8vVt0hf
Video Thumbnail
36,00000173
TIKVAH-MAGAZINE logo
TIKVAH-MAGAZINE

11 set 2026, 07:08

Photo
🔥 ታላቅ የቅድመ-ሽያጭ ቅናሽ — ቡልጋሪያ!

​በካዛንቺስ እና እንግሊዝ ኤምባሲ ያሳየነውን ስኬት ተከትሎ፣ በቡልጋሪያ የሚገኘውን አዲሱን ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ለመጀመሪያዎቹ 10 ደንበኞች በ 25% ቅናሽ ይዘንላችሁ ቀርበናል!

​የቤት እና የንግድ ሱቅ አማራጮች፦

👉 ​1 መኝታ (81 ካሬ)፦ ቅድመ ክፍያ (10%) 732,066 ብር | ሙሉ ክፍያ 7,320,662 ብር (100% ላጠናቀቀ፦ 5,490,496 ብር)

👉​ 2 መኝታ (111 ካሬ)፦ ቅድመ ክፍያ (10%) 999,757 ብር | ሙሉ ክፍያ 9,997,573 ብር (100% ላጠናቀቀ፦ 7,498,179 ብር)

👉​ 3 መኝታ (169 ካሬ)፦ ቅድመ ክፍያ (10%) 1,639,541 ብር | ሙሉ ክፍያ 16,395,410 ብር (100% ላጠናቀቀ፦ 12,296,557 ብር)

👉​ የንግድ ሱቆች (25 - 75 ካሬ)፦ ከ 3 ሚሊዮን ብር ጀምሮ

🏢  ​የክፍያ እና የህንፃው ልዩ ባህሪያት፦

🏦 ​የባንክ ብድር፦ 50% በባንክ በ20 ዓመት ረጅም ጊዜ ክፍያ ተመቻችቷል።

​📌 በPost-Tensioning ቴክኖሎጂ የተገነባ፣ ዋና ገንዳ፣ ጂም፣ ስፓ፣ የልጆች መጫወቻ እና ማራኪ የከተማ እይታ ያለው።

​🚀 ዕድሉ ሳያመልጥዎት አሁኑኑ ይመዝገቡ!
📞 ስልክ፦ 0919994818
28,4000028

Showing 30 of 73 posts

Valutazione

Accesso richiesto

Frequently Asked Questions

Di cosa parla il canale Telegram TIKVAH-MAGAZINE?+

TIKVAH-MAGAZINE (@tikvahethmagazine) è un canale Telegram elencato in Religione su tgdio. Questo profilo mostra classifica, valutazioni, recensioni e post recenti così puoi decidere prima di iscriverti su Telegram. Al momento elenca circa 193.396 iscritti su tgdio.

Come mi unisco a TIKVAH-MAGAZINE (@tikvahethmagazine) su Telegram?+

Apri il profilo del canale su tgdio, poi usa Join / Open in Telegram per andare su @tikvahethmagazine nell’app o sul web di Telegram e iscriverti gratis.

TIKVAH-MAGAZINE è un buon canale Religione?+

Su tgdio puoi controllare valutazione, recensioni, classifica e ultimi post di TIKVAH-MAGAZINE prima di unirti. Al momento elenca circa 193.396 iscritti su tgdio. Confrontalo con canali Religione simili.

Dove vedo le statistiche e i post di TIKVAH-MAGAZINE?+

Su tgdio, apri la pagina @tikvahethmagazine per statistiche iscritti, classifica, valutazioni e post recenti. Usa il link Stats per grafici di crescita e attività.